የድጅታል ኢትዮጵያ ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ካሁን ቀደም ካስመዘገብናቸው ስኬቶች የተነሳና ወደፊት ልንደርስባቸው የሚገቡ ትልሞችን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መስሪያቤት ሠራተኞች በአገራዊ የድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጅ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው። የስትራቴጂ ሰነዱ ይዘት በትኩረት መስኮች፣ የትግበራ ሂደቶች ከሚጠበቁ ውጤቶችና ታሳቢዎች መነሻ ተደርጎ ለሠራተኞች ገለጻ ተደርጓል። ሠልጣኞች የስትራቴጂው መነሻዎች፣ ዝርዝር ይዘቶችና ግልጽነት ለሚያስፈልጋቸው ነጥቦች፣ ቅንጅታዊ አሠራሮችንና ለትግበራ ልንከተለው ስለሚገባ አካሄድ በማንሳት ጥያቄና አስተያየት […]